Lo sentimos. Aún no hemos traducido esta página al español. Avísenos si desea que esto sea una prioridad y traduciremos la página lo antes posible.


We're sorry. We have not yet translated this page into Spanish. Please let us know if you want us to make it a priority and we will work to translate it as soon as possible.


Solicitar traducción Request translation

Gracias, su solicitud ha sido presentada. Thank you, your request has been submitted.

በዚህ ገጽ ላይ

የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች  | ተከፋይ ቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ | ስራዎች እና ስልጠና

 


የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች

በ 800-410-0758 በመደወል ያመልክቱ። በአማርኛ እርዳታ ለማግኘት ኤክስቴንሽን 14 ይደውሉ (ተርጓሚዎች በነጻ ይገኛሉ)። መስማት የተሳናቸው፣ መስማት የማይችሉ፣ ወይም መናገር የማይችሉ በ 711 ላይ ለዋሽንግተን ሪሌይ አገልግሎት(Washington Relay Service) ይደውሉ።

               

ቁጥሩን ሲደውሉ፣ በእንግሊዝኛ ይህንን መልእክት (wav ፋይል) ሊሰሙ ይችላሉ። እንዲህ ይላል:

"በጥሪዎች ብዛት ምክንያት ፣ በዚህ ሰዓት ጥሪዎን መቀበል አንችልም። እባክዎን በኋላ መልሰው ይደውሉ፣ ወይም የሥራ አጥነት መረጃን በዌብሳይታችን www.esd.wa.gov ላይ ይግኙ። ስለ ትግስትዎ እናመሰግናለን። ደህና ይሁኑ።"

 

የቱንም ያክል ከፍተኛ የጥሪ መጠን ቢኖርም እርስዎን ለመርዳት ቁርጠኞች ነን። የቋንቋ አስተርጓሚዎች አሉን። በስልክ ማመልከት ከፈለጉ እነዚህ ምክሮች ሊረዱዎት ይችላሉ።

  • አስቀድመው ወይም ወደ ኋላ ላይ ይደውሉኦፕሬተርን የማግኘት እድሎችዎን ይጨምሩ።
    የይገባኛል ጥያቄዎች ማእከል ሰዓቶች እና መረጃ
  • ስልኩን ይመልሱ። እኛ ልንሆን እንችላለን! ስማችን በእርስዎ የደዋይ መታወቂያ ላይ አይታይም። ጥሪያችንን ካጡ፣ መልሰው ሊደውሉልን ይገባል፣ ይህም በማመልከቻ ሂደትዎ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ይጨምራል።

  

ከማመልከትዎ በፊት:

  • የዩኤስ ዜጋ ካልሆኑ አሁንም ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ማመልከት ይችላሉ። ስለ ዜግነት እና የመስራት ህጋዊ መብትዎ የበለጠ ይወቁ
  • ስለ ኢ-ሰርቪሶች የቅጥር ዋስትና መምሪያ (Employment Security Department’s) ደህንነቱ የተጠበቀ የድህረ-ገጽ የበለጠ ለማወቅ መመሪያ ይጠቀሙ። ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ለማመልከት፣ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ለማቅረብ እና ስለ ጥቅማ ጥቅሞችዎ መረጃ ለማግኘት eServices ይጠቀሙ።

  

ማመልከቻ:-

  

ካመለከቱ በኋላ:

  • ከእኛ የውሳኔ ደብዳቤ ከተቀበሉ እና በውሳኔው ካልተስማሙ፣ ይግባኝ ለማለት ቀላሉ መንገድ በኢ-ሰርቪሶች ውስጥ በበይነ መረብ በኩል ነው። ወይም፣ የጥቅማጥቅሞች ይግባኝ ቅጹን መጠቀም ይችላሉ።
  • ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ሥራ መፈለግ አለቦት። ስለ ሥራ ፍለጋ መስፈርቶች የበለጠ ይረዱ
  • ለሠራተኞች የተለያዩ መገልገያዎችን ለማግኘት ወደ ሥራ መመለሻ ገጽን ይጎብኙ።
  • ስራን እምቢ የማለት ገጽ ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንደማይመለሱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል።
  • ትርፍ ክፍያ የሚፈጸመው አንድ ሰው ጥቅማጥቅሞችን ሲቀበል እና በኋላ ለጥቅማጥቅሙ ብቁ ሳይሆን ስናገኘው ነው። እባክዎ የትርፍ ክፍያ ማስታወቂያዎችን ችላ አይበሉ።

  

ክፍያ ያለው የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ (Paid Family & Medical Leave)

 

ክፍያ ያለው የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ (Paid Family & Medical Leave) ለዋሽንግተን ሰራተኞች የሚሰጥ ጥቅም ነው። ከባድ የጤና እክሎች እንዳይሰሩ ሲከለክልዎት ወይም የቤተሰብ አባልን ለመንከባከብ ጊዜ ሲፈልጉ፣ ከአዲስ ልጅ ጋር ግንኙነት ሲፈጥሩ ወይም በውጭ አገር ለውትድርና አገልግሎት ከሚዘጋጅ የቤተሰብ አባል ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እዚህ አለልዎት።

 

ክፍያ ስላለው ፈቃድ (Paid Leave) የበለጠ ይረዱ።

 

ስራዎች እና ስልጠና (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)

WorkSource ቀጣዩን ተግባርዎን ወይም ስራዎን እንዲያገኙ ይረዳዎታል። ለመጀመር ወደ WorkSourceWA.com ይሂዱ። በሪሶርስስ (Resources) ስር፣ በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቢሮ ለማግኘት እና ምን አይነት አገልግሎቶች በቨርቹዋል እና በአካል እንደሚገኙ ለማየት የWorkSource locator (የሥራ ምንጭ ጠቋሚ) አመልካች ይጠቀሙ።